Christian Icons

Monday, February 7, 2011

ክርስትና

  ክርስትና

     By Abebaw

ክርስትና ህይወት ናት - የሚያምኑባትን ለዘለአለማዊ ህይወት ታበቃለችና።
ክርስተና እረፍት ናት - የሚያምኑባት በምድርም ይሁን በሰማይ በክርስቶስ በኩል ባላቸው እምነት ያርፋሉና።
ክርስትና ፍቅር ናት - ለእኔ የሚያስፈልገኝ ለወንድሜም አስፈላጊው ነው ብላ ታስተምራለችና።
ክርስትና እውነት ናት - ከአንዱ ከእውነተኛው አምላክ ከእግዚአብሔር ተገኝታለችና፤ ነቅና ጥርጥረ አይገኝባትም።
ክርስትና ንጹህ ናት - ከአለም እርኩሰት ተለይታ ትኖራለችና።
ክርስትና ልዩ ናት - በስራዋ የሚስተካከላት በህይወቷም የሚወዳደራት የለምና ።
ክርስትና ብርሃን ናት - በጨለማ ላሉ የወንጌልን ብርሃን ታበራለችና። በብርሃን ላሉት ደግሞ መብራታቸው የበለጠ እንዲበራ ዘይትን ትጨምርላቸዋለችና ።
ክርስትና ፍትህ ናት - በሐብትና በመልክ በስልጣንና በጉልበት ሳይሆን ለሁሉ እንደየስራው ትከፍላለችና።
ክርስትና ትሁት ናት - የእውቀትና የስልጣን ሁሉ ምንጭ አንዱ እግዚአብሔር ነው ብላ ታስተምራለችና።
ክርስተና ምንጭ ናት - የተጠሙ ሁሉ ወደ እርሷ መጥተው ቃሉን ጠጥተው ይረካሉና
ክርስተና እሳት ናት - ከሀዲያን ; አስመሳዮችንና ስሟን የሚያጠፏትን በመጨረሻ ለመቃጠል ትሰጣቸዋለችና
ክርስትና ሰላም ናት - በእርሷ ዘንድ ጸብና ጭቅጭቅ የለምና
ክርስተና ፈተና አላት -ሰይጣን በልዩ ልዩ መንገድ በእየ ቀኑ ይፈትናታልተና
ክርስትና መሰናከያ ድንጋይ ናት - ብዙዎች ሩጫ ጀምረው ሳይጨርሱ ቀርተዋልና ::
ክርስትና የዛሬ ናት - ነገ የት እንደምትሆን ምን እንደሚያገኝህ አታውቅም የመዳን ቀን ዛሬ ነው ብላ ታስተምራለችናለ።
ክርስትና የክርስቶስ ክርስቶስም የክርስትና። ክርስቶስ የአንዲት ቤተ ክርስቲያን አንዲት ቤተ ክርስቲያንም የክርስቶስ። የቀደመችውንና ትክክለኛዋን መንገድ ለመራን ለክርስቶስ ክብር ምስጋና ይሁን
በህይወቴ በዘመኔ
ደስ የሚለኝ ለእኔ
በወንጌል ማመኔ

ይህች የክርስቶስ የሆነችዋ ቤተ ክርስቲያንም /ክርስትና /
አንዲት ናት - አቻና ወደር የላትም ብቻዋን ትኖራለች እንጂ
ቅድስት ናት - ወደ እርሷ የሚመጡትን በሙሉ በትምህርቷ ትቀድሳለችና
የሁሉም ናት - የተወሰነ ዘር ወይም ህዝብ አይደለችም ወደ እርሷ የሚመጡትን ሁሉ ያለምንም ወገናዊ አድልኦ ትቀበላለችና
ዓለም አቀፋዊት ናት - በዚህ ቦታ ብቻ የተወሰነች ናት አይባልም የእግዚአብሔር መንፈስ ባለበት የእግዚአብሔር ሰዎች ባሉበት ቦታ ሁሉ አለች እንጂ
ጥልቅ ናት - በስጋዊ ህይወት በስጋዊ እውቀት አትመረመርም። በመንፈስ የሆኑ ያውቋታል ይሄዱባትል እንጂ
የገሃነም ደጆች አይችሏትም - የሐሰት ትምህርት፤ ስጋዊያን ሰዎችም ሊያጠፋት አይችልም። ይልቁንም እነርሱ ከእርሷ እየራቁ ይሄዳሉ እንጂ
በፈተና የጸናች ናት - የተፈተነ ሊቀ ካህናት ስላላት በፈተና ሁሉ ይረዳታልና

        ቤተ ክርስቲያን ባህረ ጥበባት /2/
        አትመረመርም /2/ እጂግ ጥልቅ ናት

                                        
                                             ወስብሐት ለእግዚአብሔር 

                                 

1 comment:

  1. የገሃነም ደጆች አይችሏትም - የሐሰት ትምህርት፤ ስጋዊያን ሰዎችም ሊያጠፋት አይችልም። ይልቁንም እነርሱ ከእርሷ እየራቁ ይሄዳሉ እንጂ

    ReplyDelete

Thanks for visithing "Abebaw"